ባህላዊ ፍ/ቤት ለዘመናት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ሚዛናዊ ፍትህ እንዲሰፍን የጎላ ሚና ሲጫወት መቆየቱ ተገለጸ

You are currently viewing ባህላዊ ፍ/ቤት ለዘመናት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ሚዛናዊ ፍትህ እንዲሰፍን የጎላ ሚና ሲጫወት መቆየቱ ተገለጸ

AMN – ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ቢሮ የተዘጋጀ የባህላዊ ፍ/ቤት ለማህበራዊ ፍትህ በሚል መሪ ቃል 43ኛው የጉሚ በለል ውይይት ተካሂዷል።

ባህላዊ ፍርድ ቤት በተፈጥሮ በማህበረሰቡ መካከል የተፈጠሩ እኩልነቶችንና ፍትህን ጠብቆ ለማቆየት አስችሏል ያሉት የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ፤ ይህንንም የቀደመ እሴታችንን ለማህበራዊ ፍትህ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ጋዛሊ አባ ስመል በበኩላቸው በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ባህላዊ ፍ/ቤት በማህበረሰቡ ውስጥ ፍትህን በማስፈን ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል።

በዓለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review