የዓለም ጤና ድርጅት ከ3 ወራት በኋላ የመጀመሪያው የህክምና ድጋፍ ለጋዛ አደረገ

You are currently viewing የዓለም ጤና ድርጅት ከ3 ወራት በኋላ የመጀመሪያው የህክምና ድጋፍ ለጋዛ አደረገ

AMN- ሰኔ 20/2017

2ሺ ዩኒት ደም፣ አንድ ሺ 500 ዩኒት ፕላዝማ እና አስፈላጊ የህክና ቁሳቁሶችን የጫኑ ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች ጋዛ መድረሳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገልፀዋል፡፡

በጋዛ ከሚገኙ 36 ሆስፒታሎች መካከል 17ቱ ብቻ በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፤ በመሆኑም በቀጣይ ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ላለባቸው ሆስፒታሎች ድጋፉ ይዳረሳል ብለዋል፡፡

ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ መሰል የጤና ድጋፎች ያለ ምንም ገደብ እና በሁሉም የመግቢያ በሮች ወደ ጋዛ ሊገቡ እንደሚባም አሳስበዋል፡፡

በሌላ ዜና እስራኤል ባደረሰችው ሁለት የአየር ጥቃቶች 18 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶችም መቁሰላቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል፡፡

ይህ የእስራኤል ጥቃት የተሰማው በአሜሪካ የሚደገፉ የዐረብ አሸማጋዮቹ ግብፅናፅ ኳታር በእስራኤልና ሀማስ መካከል አዲስ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ ከጫፍ በደረሱበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ጋዛን ለሁለት አሥርታት የገዛው ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች ሊለቅ እና ጦርነቱ እንዲያበቃም የጦር መሳሪያ ሊያስቀምጥ እንደሚገባ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያም ኔታንያሁ ተናግረዋል፡፡

ሀማስ በበኩሉ እስራኤል ዘላቂ ተኩስ አቁም ካደረገች እና ጋዛን ለቃ ከወጣች ሁሉንም ታጋቾች እለቃለሁ ሲል ይደመጣል፡፡

እስካሁን ድረስ በእስራኤል ጥቃት ከ56 ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ሕይወት ሲያልፍ በሀማስ ሚሊሻዎች ደግሞ አንድ ሺ 200 እስራኤላዊያን ተገድለዋል፡፡

251 የሚሆኑ እስራኤላውያን ታግተው የነበረ ሲሆን አብዛኖቹ በሀማስና እስራኤል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር መለቀቃቸውም የሚታወስ ነው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review