ኢትዮጵያ በአስደናቂ የህዳሴ ጉዞ ላይ ትገኛለች ሲሉ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወቃል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያን አስደናቂ ቅርሶችና ታሪኳን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ታድሶ ለዕይታ ክፍት የሆነውን ብሔራዊ ቤተመንግሥትንም ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸውን በተመለከተም በይፋዊ የክብር መዝገብ ላይ ባሰፈሩት የማስታወሻ መልዕክት ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ ህያው ታሪክ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ ሀገር መሆኗን ያወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፥ በአስደናቂ የህዳሴ ጉዞ ላይ ትገኛለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ድንቅ የታሪክ ጸጋና ታላቅ ሀገርነት ኩራት እንደተሰማቸውም ነው በመልዕክታቸው የጠቀሱት።