በመዲናዋ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች የደን ሽፋኑን ከማሳደግ በተጨማሪ የስራ ዕድልም የፈጠሩ መሆናቸው ተገለፀ

You are currently viewing በመዲናዋ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች የደን ሽፋኑን ከማሳደግ በተጨማሪ የስራ ዕድልም የፈጠሩ መሆናቸው ተገለፀ

AMN- ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች የከተማዋን የደን ሽፋን 20 በመቶ ከማድረሱ በተጨማሪ፣ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ማህበራት የስራ ዕድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል::

አዲስ አበባ ከተማ እንደ ዓለም ዓቀፍ ከተማነቷ በቂ የደን ሽፋን እንዳልነበራት እና የነበራት የደን ሽፋንም ከ2.8 በመቶ በታች እንደነበር የአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለዘመናት ትኩረት ተነፍጎት የነበረው የከተማዋ የአረንጓዴ ልማት፣ እንደ ሀገር በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ላለፉት ስድስት ዓመታት በከፍተኛ የህዝብ እና የተቋማት ንቅናቄ በመተግበሩ ከተማዋ የነበራትን የደን ሽፋን ወደ 30 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡

እንዲሁም ከተማዋ ለነዋሪዎች ምቹና ፅዱ አረንጓዴ ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ከተማ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከ60 ሚሊየን በላይ ችግኝ እንደ ከተማ መተከሉን የገለፁት ኃላፊው፣ ከመትከል ባለፈ በ2016 እና በ2017 ዓ.ም የተተከሉ ችግኞች የፅድቀት መጠን 88.2 በመቶ መሆኑን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በሶስተኛ ወገን በተደረገ ቁጥጥር መረጋገጡንም አንስተዋል፡፡

እንደ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በተከናወኑ ስራዎች የዓለም ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል እና ስነ-ምህዳር ጋር የተጣጣመ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ እንደሻው፣ በቢሮ በረጃ ከስድስት ሺህ በላይ ዜጎች ከ600 በላይ በሆኑ ማህበራት ተደራጅተው ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በመስራት የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

አንደ ከተማ ከሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በተጨማሪ በኮሪደር ልማት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት የከተማዋን የአረንጓዴ ልማት ሽፋን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ውጤቶች መገኘታቸውንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

#AMN

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review