ጥምር የፀጥታ ኃይል በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

You are currently viewing ጥምር የፀጥታ ኃይል በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

AMN ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ጥምር የፀጥታ ኃይል በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አካሄዷል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ የፌደራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያና በ26ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባለት ምልመላ ዕቅድ ላይ ውይይት ማካሄዳቸዉን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ውይይቱን በመሩበት ወቅት አሁን ላይ የሀገራችን የፀጥታ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየተለወጠ ማምጣቱን ተናግረው ሀገራችንን የሚመጥን የፀጥታ ስምሪት በማካሄድ ኢትዮጵያ ሙሉ አቅሟን በልማት ላይ እንድታውል ሁሉም የፀጥታ አካላት ትኩረት ሰጥተው መረባረብ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ኅብረተሰቡ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር በባለቤትነት ጭምር ሰላምና ፀጥታን ለማስከበርና የወንጀል ስጋቶችን ለመከላከል እየሠራ መሆኑን አንስተው የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር በማክሸፍ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ነውም ብለዋል፡፡

በአራቱም የሀገራችን ማዕዘናት ፍተሻዎችን በማጠናከር ሕገ-ወጥ የሰውና የጦር መሣሪያ፣ የማዕድን፣ የኮንትሮባንድ፣ የአደገኛ ዕፅ እና ሌሎች መሰል የወንጀል እንቅስቀሴዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ኮሚሽነር ጀነራል ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ የፀጥታ ስምሪት በማካሄድ እና የትራፊክ ደኀንነትን በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና መወጣት እንዳለበት ኮሚሽነር ጀነራል ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል በቀጣይ በ Leadership Challenges ዙሪያ ክልሎችን ያሳተፈ የውስጥ ስልጠና ለመስጠት በጋራ እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሪሮርም ሥራዎች የደረሰበትን የቴክኖሎጂ አቅም ወደ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ለማስፋፋት በጋራ በመቀናጀት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የ26ኛ ዙር መሠረታዊ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምልመላ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ምልመላው ከአሁን በፊት ከነበረ በተሻለ ሁኔታ የብሔር ብሔረሰቦችን እና የፆታን ተዋፅኦ ባካተተ መልኩ መከናወን እንዳለበት የሥራ መመሪያ ሰጥቸዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review