የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሜሪካ የመጀመሪያ ፍርድ ቤቶች የከፍተኛ ባለስልጣናትን ትዕዛዝ የማገድ ስልጣናቸውን መገደቡ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ለቀጣይ ፕሬዝዳንቶች ታላቅ ድል ሆኗል።
ትራምፕ በዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በቤተ-መንግስቱ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁ ሲሆን ለህገ መንግስቱ፣ ለስልጣን ክፍፍል እና ለህግ የበላይነት ታላቅ ድል መሆኑን ገልፀዋል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፕሬዝዳንቱ በውልደት ዜግነት ትዕዛዝ ላይ ብቻም ሳይሆን በሌሎቹም በርካታ የፖሊሲ ተግባራቱ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይጠበቃል።
በዚህም የትራምፕ በውልደት የሚገኝ ዜግነትን የማስቀረትን ውሳኔ ከአሁን ጀምሮ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል በር ከፍቷል።
አሁንም ግን የበታች ፍርድ ቤቶች ህጋዊ በሆኑ ጉዳዮች ይህን ትዕዛዝ መገደብ የሚችሉበትን እድል ትቷል።
በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ የህግ ትግሎች የሚጠበቁ ሲሆን በጥቅምት የመጨረሻ ውሳኔው ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን