የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ስራችን ገብቶን የምንሰራው ለትውልድ የምናስተላልፈው መልካም ተግባር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ተናግረዋል፡፡
ሰባተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ባለፉት ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ስራዎች የተገኙ ውጤቶች አጠናክሮ በማስቀጠል ዘንድሮም ለትውልድ የሚሸጋገር አሻራችንን የምናስቀምጥበት እና ራስ ወዳድ አለመሆናችንን እና ነገን አሻግረን የምናይ መሆናችንን በተግባር ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል፡፡
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለልጆቻችን የሚወረስ አሻራ የማስቀመጥ ዋልታና ምሰሶ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥም በትኩረት የምንሰራበት ነው ብለዋል፡፡
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለወዳጅም ለጠላትም ገብቶን የምንሰራው ስራ መሆኑን የምናሳይበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በያለው ጌታነህ