በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላምን የሚደግፍና ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላምን የሚደግፍና ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

AMN ሰኔ 22/2017

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላምና ልማትን የሚደግፍና ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በሰላማዊ ሰልፉም የመንግስትን የልማትና የሰላም ጥረት በማድነቅ የተጠናከረ እገዛና ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ፅንፈኛው ቡድን በዜጎች ላይ የሚፈፅመውን እገታ ግድያና ዘረፋ እናወግዛለን በማለት በሰልፉ ላይ ሃሳባቸውን እየገለፁም ይገኛሉ።

የሰልፉ ተሳታፊዎች ሰላም እንፈልጋለን፣መንግስት ህግ በማስከበር የንጹሐንን ገዳዮች ለህግ ያቅርብልን፣ የልማት አርበኝነትን ለልጆቻችን እናወርሳለን፣ ሰላም የጋራ ሃብት ነው በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል፣ ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች እያሰሙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review