ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተወያዩ

AMN ሰኔ 23/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር መወያየታቸዉን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ጠዋት በሬይስ ኦፍ ሆፕ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከመጡት የአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተገናኝተናል ብለዋል፡፡

የአለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ በካንሰር ሕክምና ክብካቤ፣ የእንስሳት ጤና፣ የፀፀ ፍላይ ዝንብ ማጥፊያ፣ በኒኩለር ኢንጂነሪንግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ነው። ውይይታችን በመካሄድ ላይ ባሉ ድጋፎች እና የወደፊት የትብብር እድሎች ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review