በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአራት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው

You are currently viewing በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአራት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው

AMN ሰኔ 23/2017

በትግራይ ክልል የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ዛሬ እየተሰጠ ነው።

ፈተናውን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ያስጀመሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ናቸው ።

ፕሬዝዳንቱ ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው የሚሰጣቸውን ፈተና እንዲወስዱና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች እየተፈተኑ የሚገኙ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች 36 ሺህ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ(ዶ/ር) ናቸው።

ፈተናውን በተረጋጋ መልኩ ለማጠናቀቅም የክልልና እና የፌዴራል ፀጥታ አከላት በትብብር አሰፈላጊውን ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ተናግረዋል።

በመቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈተና እየወሰዱ ካሉት መካከል አንዳንድ ተማሪዎች እንዳሉት፣ በኩረጃ ሳይሆን በራሳቸው ጥረት ሰርተው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማለፍ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በወረቀትና በኦላይን እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review