የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ በበይነ መረብ ወይም በኦንላይን እየተሰጠ ነው

You are currently viewing የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ በበይነ መረብ ወይም በኦንላይን እየተሰጠ ነው

AMN ሰኔ 23-2017 ዓ.ም

በመላ ሀገሪቱ የሚሰጠው የ2017 የትምህርት ዘመን አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በ108 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀምሯል፡፡

የዘንድሮው ፈተና በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ወይም በኦንላይን እየተሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል ።

ተማሪዎች ሰፊ ጊዜ ተሰጥቷቸው ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት ኃላፊው አስፈላጊ ዝግጅቶች ቀድም ብለው መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል።

ሀገር አቀፍ ፈተናው በተለያዩ ዙሮች የሚሰጥ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 23 እስከ 30 ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች

ደግሞ ከሐምሌ 1 እስከ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ 51 ሺህ 259 ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናውን እንደሚወስዱ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በካሳሁን አንዷለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review