በኦሮሚያ ክልል በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ነገ ይጀመራል ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ይህንኑ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግልጫ ሰጥቷል።
በክልሉ እስካሁን በተሰሩ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ለድርቅ ተጋልጠው የነበሩ ሐይቆች ፣ ኩሬዎች እና ወንዞችን ወደ ቀድሞ ተፈጥሯዊ ይዘታቸው መመለስ እና ማንሰራራት ችለዋል ፣ ለዚህም የሐሮማያ ሐይቅ ማሳያ ነው ብለዋል ።
የአረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ ቀደም ሲል በድርቅ የሚታወቀው የሐረርጌ ተራራዎችም ወደ ፍራፍሬ ማምረቻ አካባቢ መቀየር መቻሉን እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ።
የአረንጓዴ አሻራ ኢንቬቲቭ በክልሉ ያለውን የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል ያሉት ሃላፊው ።
ባለፉት 6 አመታት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል የአረንጓዴ አሻራ ስራ ተሰርቷል የጽድቀት መጠኑም 85 በመቶ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በዚህም በምግብ ራስን መቻል ፣ የግብርና ምርት ወደ ውጭ መላክ ፣ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩንም ሃላፊው ተናግረዋል
ለ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 5 ቢሊዮን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸዉን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ገልጸዋል።
ችግኞቹን ለመትከል 1. 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል፡፡
በክልሉ የነበረው የ18 በመቶ የደን ሽፋን አሁን ላይ ወደ 29 በመቶ ማድረስ መቻሉን ኃላፊው ግልጸዋል።
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 2.5 ቢሊዮን የቡና ችግኝ መዘጋጀቱንና ለሻይ ምርት በልዩ ትኩረት የሚሰራ ይሆናል ገልፀዋል ።
በዳንኤል መላኩ

See insights and ads
All reactions:
2727