ችግኝ በመትከል ዓለምን እያከምን ነው ስትል ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሃሴት ደረጄ አድማሱ ተናገረች

You are currently viewing ችግኝ በመትከል ዓለምን እያከምን ነው ስትል ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሃሴት ደረጄ አድማሱ ተናገረች

AMN ሰኔ 23-2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛውን ሀገር ዓቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ዓለም ዓቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ትላንት በከተማ ደረጃ ማስጀመሩ ይታወቃል።

በመርሃ ግብሩ ከተሳተፉ ኢትዮጵያውያን መካከል በዓለም ዓቀፍ የቁንጅና ውድድር መድረክ የሃገሯ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲታይ በማድረግ በዓለም ሁለተኛ እንዲሁም በአፍሪካ ቀዳሚ መሆን ያሸነፈቸዉ ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሃሴት ደረጃ ትገኝበታለች።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የምንኮራበት ባህላችን ልናደርገው ይገባል ብላለች።

ኢትዮጵያ ለምለም ምድር ያላት ሃገር ነች ያለችው ሃሴት፤ ይህንን አስጠብቆ ለመቀጠል በዚህ መርሃ ግብር በመሳተፌ ደስተኛ ነኝ ብላለች።

ለራሳችን እና ቀጣይ ትውልድ እንዲሁም ለልጆቻችን የምናስረክባትን ኢትዮጵያ ነው እየሰራን ያለነው ስትልም ተናግራለች።

ይህ ከአዳራሽ አጀንዳ ባለፈ ዓለምና ምድርን የምናክምበት ትልቅ ስራ ነው፤ ስለሆነም ይህንን ለነብሳችን የሚሆን ስራ ልንሰራ ይገባል ስትል መልእክቷን አስተላልፋለች።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review