የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮሪደር ልማት እና በእርጅና ምክንያት በፈረሰዉ ህንፃ ምትክ ያስገነባውን ሁለገብ ህንጻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት የምርቃት ስነስርአት ላይ ለቤተክርስቲያኗ አስረክበናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ሁለገብ ህንፃዉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት በመባል በሚታወቀዉ የቤተክርስቲያኗ ይዞታ ላይ የተገነባ መሆኑንም ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
አክለውም በከተማ አስተዳደሩ በጀት ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በዛሬዉ ዕለት የተመረቀዉ ህንፃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ነዉ ብለዋል፡፡