የአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ተፈጥሮን ከነዋሪዎች ያወዳጀ ፕሮጀክት ነው- አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት

You are currently viewing የአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ተፈጥሮን ከነዋሪዎች ያወዳጀ ፕሮጀክት ነው- አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት

AMN – ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የተካሄደው 7ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ማስጀመራቸው ይታወቃል።

በማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰበ አካላት ተሳትፈዋል ።

አሻራቸውን በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት ተሳታፊዎቹ መላው ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነ ባለበት በዚህ ወቅት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፈተናውን ለመቀልበስ ጉልህ ድርሻ አለው ነው ያሉት ።

የተተከሉ ዛፎች የአየር ሙቀትን ለመከላከል እንዲሁም ለምግብነት መዋል ጨምሮ አገልግሎታቸው ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ዲፕሎማቶቹ አሻራቸውን በማኖራቸው የፈጠረባቸውን ስሜት ገልፀው መርሃ ግብሩ ለመጪው ትውልድ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል ።

በአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ለአፍሪካም ሆነ ለተቀረው ዓለም ምሳሌ መሆን ችላለች፣ በተለይም የተበከሉ ወንዞችና ዳርቻዎች ዳግም ለምተው የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ተፈጥሮና ነዋሪዎችን እንዲዛመድ ማድረግ ችላለች ነው ያሉት።

ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንዳቸው ደማቅ የጋራ ታሪክን እያኖሩ የሚገኙበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review