በራሪዉ ሰው መሰል ሮቦት

You are currently viewing በራሪዉ ሰው መሰል ሮቦት

AMN – ሰኔ 25/2017 ዓ.ም

ላለፉት ጥቂት ዓመታት የጣሊያኑ የቴክኖሎጂ ምርምር ተቋም በአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ ሮቦት ለመስራት ሲሞክር ቆይቷል።

በመጨረሻም ተቋሙ የመጀመሪያ የሆነውን አየር ላይ መንሳፈፍ የሚችል ሰው መሰል ሮቦት መፈብረክ መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል።

የጣሊያኑ የቴክኖሎጂ ተቋም ሃላፊ ዳንኤሌ ፑቺ፤ እንደዚህ አይነት ሮቦቶች እንደ መሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ያሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት እሳትና ጎርፍ ሳይገድባቸው በአየር ላይ በመንሳፈፍ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዲደርሱ ለማስቻል ታስቦ መሰራቱን ገልፀዋል።

ሮቦቱ 4 የጀት ሞተሮች እና 4 አካባቢውን ሁኔታ የሚዳስሱ ሴንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን እስከ 800 ዲ.ሴ ድረስ ሙቀትን መቋቋም እንዲችል ተደርጎም የተሰራ ነው።

በሙከራው ወቅት ተስፋ ሰጪ የሆነ ውጤት ማየታቸውን የተናገሩት ተመራማሪዎች ከሚበረው ሮቦት በተጨማሪም ለእርዳታ ፈላጊዎች ምግብ፥ መድሃኒት እና ቁሳቁሶችን ማጓጓዝ የሚችሉ ሳጥኖችንና ሌሎችንም የመስራት ሃሳብ እንዳላቸውም ገልፀዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review