የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ ህብረ ብሄራዊ አንድነትንና ወንድማማችነትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

You are currently viewing የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ ህብረ ብሄራዊ አንድነትንና ወንድማማችነትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

AMN ሰኔ 24/2017

የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ ህብረ ብሄራዊ አንድነትንና ወንድማማችነትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የሰላም፤ የልማትና የአንድነት ህዝባዊ ኮንፍራንስ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄዷል፡፡

“ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደዉ ኮንፍራንስ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እንዲሁም ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ተወላጆች፤ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም ዞኖች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ክልሉ በታሪክ በባህልና በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ታሪክ በባህልና በተፈጥሮ ሀብት የሰባ እምቅ አቅም ያለውን ክልል በሰላም እና በአንድነት ግንባር ቀደም መሆን እንዲችል የተጀመረውን አዎንታዊ ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል እንዲቻል አንደ ብልፅግና ፓርቲ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ ህብረ ብሄራዊ አንድነትንና ወንድማማችነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት መሆኑን በማንሳት የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ እዉን ለማድረግ በአብሮነትና በወንድማማችነት መንፈስ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የርእሰ መስተዳድሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ሃላፊ ኤደን ንጉሴ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት ዉይይቱ የውስጥ አንድነትን ይበልጥ በማጠናከር ለክልላዊና ሀገራዊ ሰላም፤ ልማት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ግብ በጋራ ለመረባረብ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነዉ ብለዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ከዉይይቱ ማጠቃለያ በኋላ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸዉንም የርእሰ መስተዳድሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ሃላፊ ኤደን ንጉሴ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review