የ2018 የፌዴራል መንግሥት በጀት 1.93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

You are currently viewing የ2018 የፌዴራል መንግሥት በጀት 1.93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

AMN- ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት አዋጅ ለዝርዝር እይታ እና ምርምራ መመራቱ ይታወሳል።

ፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴውም የቀረበውን ረቂቅ በጀት አዋጅ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤትም የቀረበውን 2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1390/2017 ሆኖ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

በዚህም የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 1.93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

ለ2018 በጀት ዓመት ከፀደቀው በጀት ብር 1.93 ትሪሊዮን ውስጥ የመደበኛ ወጪ 1.2 ትሪሊዮን ወይም 61.4 በመቶ፤ ለካፒታል ወጪ ብር 415.2 ቢሊዮን ወይም 21.6 በመቶ፤ ለብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ብር 315 ቢሊዮን ወይም 16.3 በመቶ፤ ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ብር 14 ቢሊዮን ወይም 0.7 በመቶ የበጀት ድርሻ ይዘዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review