በበጀት ዓመቱ 4.5 ሚሊየን ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ 4.5 ሚሊየን ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN- ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሥራ አጥነትን ከመቅረፍ አኳያ በሰጡት ማብራሪያም፣ በበጀት ዓመቱ 4.5 ሚሊየን ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዘርፉ ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት እንደሆነ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በግብርና 1.8 ሚሊየን እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 1.6 ሚሊየን የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከሌሎች ዘርፎች አንፃር 39 እና 36 በመቶ ድርሻ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ስራ ስምሪት ከ5 መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review