በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN- ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል፡፡

በድምሩ 3 መቶ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች መፅደቃቸውን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አጠቃላይ ወጪውም 1.5 ትሪሊየን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፀደቁ ፕሮጀክቶችም ውስጥ 169 ገደማ የሚሆኑትና 11 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ግንባታ መጀመሩንና በዘንድሮው በጀት ዓመትም 1 ሺህ ኪሎ ሜትሩ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ 17 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚይዙ 145 የጥገና ፕሮጀክቶችም እንደተጀመሩ እና በመገባደድም ላይ ያሉም እንዳሉ አብራርተዋል፡፡

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review