የዲያጎ ጆታ ህልፈትን ተከትሎ በርካቶች ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ

You are currently viewing የዲያጎ ጆታ ህልፈትን ተከትሎ በርካቶች ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ

AMN- ሰኔ 256/2017 ዓ.ም

የሊቨርፑል ተጫዋች የነበረው ዲያጎ ጆታ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ክለቦች እና ተጫዋቾች ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛል።

በስፔን የደረሰውን የሚኪና አደጋ የተከሰተው ጎማ በመፈንዳቱ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል።

ጆታ ያሽከረክራት በነበረችው “ላምቦርጊኒ” መኪና ውስጥ የነበረው ወንድሙ አንድሬ ሲልቫም ሕይወቱ እንዳጣ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።

መረጃው ከተሰራጨ በኋላ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ጨምሮ የቡድን አጋሮቹ ፣ በተቃራኒ የገጠማቸው ተጫዋቾች ጭምር ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው።

የቀድሞ አሰልጣኘ የርገን ክሎፕ ’’የዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬ ህልፈት ልቤን በሀዘን ሰብሮታል፤ ዲያጎ ድንቅ ተጫዋች ብቻ አልነበረም ግሩም ጓደኛ እና በፍቅር የተሞላ ልብ ያለው ባል እና አባት ነበር፤ ሁሌም ትናፍቀናለህ’’ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአል ሂላል እየተጫወተ የሚገኘው ሩበን ኔቬስ ግን በሃዘን ተጎድቷል ተብሏል። በዓለም የክለቦች ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የሳውዲው ክለብ ነገ ከፍሉሚኔንሴ ጋር ይጫወታል።

የአል ሂላል አሰልጣኝ ቡድን አባላት ምንም አይነት ውሳኔ ቢወስን ከጎኑ እንደሚሆኑ አረጋግጠውለታል።

ምናልባት በጨዋታው መሰለፍ የሚያስችል አእምሯዊ ዝግጁነት ከሌለው ፍቃድ ሊሰጡት ይችላል ተብሏል።

የሊቨርፑል ደጋፊዎችም ዲጎ ጆታን ለማሰብ በአንፊልድ አቅራቢያ እየተሰባሰቡ ይገኛሉ፡፡

ደጋፊዎች ለዓመታት የዘመሩለት ፖርቹጋላዊ አጥቂን ህልፈት አምነው ለመቀበል ተቸግረዋል፡፡

በአንፊልድ አቅራቢያ በመሰባሰብ በተለያየ መንገድ ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛለሉ፡፡

የሦስት ልጆች አባት የነበረው የ28 ዓመቱ ዲያጎ ጆታ ከአምስት ቀናት በፊት ነበር ሰርግ የደገሰው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review