መዲናዋን የሚመጥን የሰላምና ፀጥታ ስራ መሰራቱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሰታወቀ

You are currently viewing መዲናዋን የሚመጥን የሰላምና ፀጥታ ስራ መሰራቱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሰታወቀ

AMN- ሰኔ 26/2017

አዲስ አበባ ትክክለኛ አለምአቀፍ የዲፕሎማቲክ ከተማነቷንና የሀገሪቱ መዲና መሆኗን የሚመጥን የሰላምና ፀጥታ ስራ መሰራቱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በርካታ አለም አቀፍ ጉባኤዎችን የምታስተናግደው አዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ለውጥ ላይ መሆኗንና ፍፁም ሰላማዊ ከተማ መሆኗን ተናግረዋል።

በከተማዋ የሽብር ድርጊት ሊፈፅሙ የነበሩ የፀረ ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር ማክሸፍ መቻሉንና የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል ላይ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱንም ገልጸዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የህግ የበላይነትን በማስከበር ከተማዋ ፍፁም ሰላማዊ እንድትሆንና በተረጋጋ ሁኔታ የልማት እንቅስቃሴዋን እንድታሳልጥ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ህገ ወጥነትን መከላከል፣ ወንጀለኞች እንዲያዙ በማድረግ፣ አዋኪ ድርጊቶችን በመግታት ፣ ህጋዊ የሆነ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እንዲሁም ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ በማድረግ ረገድ የሰላም ሰራዊቱ የነበረው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል።

የመረጃ ስርዓት አያያዝን ቀልጣፋና ፈጣን በማድረግ በ7/24 የስራ ባህል ህገ ወጥነትን እየተከላከልን ነው ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር እና ከአጎራባች ሸገር ከተማ ጋር ስራዎችን በጋራ በመስራት ለውጦች መመዝገባቸውን አብራርተዋል።

ከተማዋ ትክክለኛ አለምአቀፍ የዲፕሎማቲክ ከተማነቷንና የሀገሪቱ መዲና መሆኗን የሚመጥን የሰላምና ፀጥታ ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።

በደሳለኝ ሙሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review