ኢትዮጵያ በኢንተርፖል ንቁ አባል ሆና መቀጠሏን የኢንተርፖል ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በኢንተርፖል ንቁ አባል ሆና መቀጠሏን የኢንተርፖል ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር (ዶ/ር) ገለፁ

AMN- ሰኔ 26/2017

የአለም አቀፉ የፀረ ወንጀል የጋራ ፖሊሳዊ ጥምረት ኢንተር ፖል ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ጋር በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

እንደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለፃ ኢትዮጵያ ከኢንተርፖል ጋር ባለፉት ጊዜያት የሰራችው ስራ ውጤታማ መሆኑን በውይይቱ መገለፁን ተናግረው በቀጣይም በጋራ መስራት የሚያስችል ውይይት መደረጉን አብራርተዋል።

በዋናነት የድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ሃሳቦች መነሳታቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በኢንተርፖል ውስጥ ስለሚኖራት ሚናና ድጋፍ ዙሪያ መወያየታቸውን ተናግረዋል።

የፕሬዘዳንቱ እዚህ መምጣትም ለኢትዮጵያ ፖሊስ በቀጣይ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በኢንተርፖል ንቁ አባል ሆና ቆይታለች ያሉት የዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም የኢንተርፖል ፕሬዚዳንት ሜጀር ጀነራል አህመድ ናስር (ዶ/ር)፣ በዚህም የተደራጁ ወንጀሎችን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና ነበራት፣ ይህም ለኢንተርፖል ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያሉ የሪፎርም ስራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review