ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የአፍሪካ የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም እንደምታስተናግድ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የአፍሪካ የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም እንደምታስተናግድ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ

AMN ሰኔ 27/2017

ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ ግብርናን በማዘመን የስራ ዕድል መፍጠር፣ የፋይናንስና ዲጂታል አካታችነት የሶስተኛው የአፍሪካ የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም የትኩረት ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፎረሙ አፍሪካ ያላትን ወጣት የሰው ኃይል በመጠቀም የአህጉሪቱን ልማትና ህዳሴ ማፋጠን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር አንስተዋል።

የአፍሪካ አገራት በስራ እድል ፈጠራ በተናጠል የሚያከናውኑት ተግባር እንዳለ ሆኖ በትብብር እድሎችን ለመጠቀምና ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ ሌሎች አስቻይ ሁኔታዎችን በመጠቀም ገበያና የስራ እድልን በትብብር ለመፍጠር ምክክር እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ግብርናን በማዘመንና በሌሎች ዘርፎች በስራ እድል ፈጠራ ባከናወነቻቸው ዘርፎች ልምድን የምታካፍል ይሆናል።

ኢንቨስተሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ኢንተርፕራይዞችና ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች በጉባኤው የሚገኙ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፎረሙን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንና የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ትሬድ ግሩፕ (African Electronic Trade Group ) ከተሰኘ ተቋም ጋር በመተባበር ማዘጋጀቷም በመግለጫው ተነግሯል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review