የሸገር ከተማ አስተዳደር የሸገር 2025 ዓለም አቀፍ ኢን ቨስትመንት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

You are currently viewing የሸገር ከተማ አስተዳደር የሸገር 2025 ዓለም አቀፍ ኢን ቨስትመንት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

AMN- ሰኔ 27/2017 ዓ.ም

ኤክስፖው ከሰኔ 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል መዘጋጀቱንና በመርሐ-ግብሩም ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እና ከ190 በላይ ባለሃብቶች እንደሚገኙ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የኤክስፖው ዓላማም፣ ሸገር ከተማ የጀመረችውን የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ መሆኑን ያነሱት ከንቲባው፣ ኤክስፖው በርካታ ዘርፎች የሚሳተፉበት በመሆኑ አስፈላጊ ልምዶች የሚቀመርበት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንቨስትመንት ኤክስፖውን ልዩ የሚያደርገው አርሶ አደሩን በትኩረት ያቀፈና ኢንቨስትመንቱም ውጤታማ መሆኑ፣የሥራ ዕድል የሚፈጥር እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል።

ኤክስፖውም የከተማዋን ዓለም አቀፍ ትስስር የሚፈጥርና ኢንቨስትመንትን የሚያሳድግ በመሆኑ የዘርፉ ተዋንያን እንዲታደሙም ጥሪ አቅርበዋል።

በዓለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review