ሩሲያ በአንድ ሌሊት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መሰንዘሯን ዩክሬን አስታወቀች

You are currently viewing ሩሲያ በአንድ ሌሊት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መሰንዘሯን ዩክሬን አስታወቀች

AMN- ሰኔ 27/2017 ዓ.ም

በጦርነቱ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የሩሲያ የሰው አልባ አውሮፕላኖች በተፈጸመው ጥቃት 23 ሰዎች መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የዩክሬን አየር ኃይል እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ሩሲያ በአንድ ሌሊት በ 539 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 11 ሚሳኤሎች ጥቃት ሰንዝራለች።

ጥቃቱ የተፈጸመው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን የስልክ ንግግር ካደረጉ ከሰዓታት በኋላ መሆኑን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በግጭቱ ላይ የሚደረገውን የድርድር ሂደት እንደሚያስቀጥሉ ቃል በመግባትም፣ ሞስኮ በዩክሬን ያላትን ዓላማ እንደማትተው ገልጸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ጥቃቱን ሆን ተብሎ የተፈፀመ በማለት አውግዘው ጠንካራ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠይቀዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review