የሸገር ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው “ሸገር 2025 የኢቨስትመንት ኤክስፖ ” ተከፍቷል፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰአዳ አብዱረህማንና የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ኤክስፖዉን አስጀምረዋል፡፡
ኤክስፖዉ በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የተከፈተ ሲሆን የሸገር ከተማን የኢንቨስትመንት እድሎች ለማሳወቅ ታልሞ የተዘጋጀ ነዉ፡፡
ኤክስፖው ከሰኔ 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከ190 በላይ ባለሃብቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኤክስፖዉ መክፈቻ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰአዳ አብዱረህማን; የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) እንድሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በተመስገን ይመር