የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን የአቅመ ደካሞችን ቤት እደሳ አስጀምሯል፡፡
በአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የቢሮው ኃላፊዎች እና በጎ ፈቃደኞች በተገኙበት ስራው በይፋ ተጀምሯል፡፡
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ሰላም ከመጠበቅ በተጨማሪ መሰል የበጎ ፈቃድ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የገለፁት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ በቀጣዮቹ 90 ቀናት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ13 የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት እንደሚያድሱም ተናግረዋል።
መንግስት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል ባለፉት ዓመታት ሰው ተኮር ተግባራት ማከናወኑን ያነሱት የቢሮ ኃላፊዋ፣ በዚህ ክረምትም በተመሳሳይ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር እንደ ቤት እድሳት ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።
በአሰግድ ኪዳነማሪያም