በቴክሳስ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

You are currently viewing በቴክሳስ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 28/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኬር በተባለው አካባቢ በደረሰ ከባድ የጎርፍ አደጋ እስከ አሁን የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

25 ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችም የደረሱበት አልታወቀም፡፡

ልጃገረዶች በሚገኙበት የሰመር ካምፕ ውስጥም ከ23 እስከ 25 የሚደርሱ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ እየተገለጸ ነው፡፡

እስከ አሁን 237 የሚሆኑ ሰዎችን ከአካባቢው የማስወጣት ስራ መሰራቱም ተነግሯል፡፡

የቴክሳስ ግዛት አስተዳደሪ ግሬግ አቦት አደጋውን “የተለየ ጥፋት” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ለነፍስ አድን ሰራተኞችም ሥራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲያግዝ የአደጋ ጊዜ አዋጅ መፈረማቸው ተገልጿል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች ያለ ምንም እረፍት ስራቸውን እያከናወኑ ስለመሆኑም የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የአየር ትንበያ አገልግሎት፣ በአካባቢው የዚህን ያክል መጠን ያለው ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል አለመተንበዩን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ኬንዳ በተባለ አካባቢም ሌላ የሞት አደጋ መድረሱ የተነገረ ሲሆን፣ ከጎርፍ አደጋው ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ የተባለ ነገር አለመኖሩ ተገልጿል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review