የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስገነዘበ

You are currently viewing የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስገነዘበ

AMN- ሰኔ 28/2017 ዓ.ም

ክረምቱን ተከትሎ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስገንዝቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ በየወሩ የግንዛቤ እና የጥንቃቄ መልዕክትን ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም የ2017 በጀት ዓመት መጠናቀቁን አስመልክቶ 12ኛውን እና የዓመቱን መጨረሻ የትራፊክ ሳምንት “ከትራፊክ አደጋ እራሱን የጠበቀ ትውልድ እንፍጠር” በሚል መሪ ሀሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ አካሂዷል፡፡

የትራፊክ አደጋን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች አንዱ፣ የወጡ ደንቦችን እና ህጎችን አለመተግበር መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ፖሊስ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ተናግረዋል፡፡

የእግረኞች የጥንቃቄ ጉድለትም ሌላኛው የአደጋ መንስኤ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስም ከባለድርሻ አካላት እና ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ኢንስፔክተር ሰለሞን ተናግረዋል።

ክረምቱን ተከትሎ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ አሽከርካሪም ሆነ እግረኛው ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ አሳስበዋል።

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review