የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋገጥ ወጣቱ ኃላፊነቱን በአርበኝነት ሊወጣ እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

You are currently viewing የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋገጥ ወጣቱ ኃላፊነቱን በአርበኝነት ሊወጣ እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

AMN- ሰኔ 29/2017 ዓ.ም

ያሉንን እምቅ ሀብቶች በመጠቀም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋገጥ ወጣቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአርበኝነት ሊወጣ ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

“ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሔድ የቆየው የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ በፌደራል ደረጃ በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በመድረኩ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ማእከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ለማረገገጥ በምታደርገው ጉዞ ወጣቱ ትውልድ የትስስር ትርክትን በመላበስ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የቱሪዝም ብሎም ሰፊ ቁጥር ያለው እና በችግር ጊዜ በአንድነት የሚቆም ህዝብ ያላት ሀገር ናት ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚይዘው ወጣቱ ኃይል፣ ምርታማነትን ለማጎልበት፣ የኢኖቬሽንና የፈጠራ ውጤቶች እንዲበራከቱ ብሎም ሰፊ የገበያ እድልን በመፍጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ማርሽ ቀያሪ አቅም ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረትም መንግስት ይህንን አቅም ለመጠቀም የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ጨምሮ ወጣቱን በትምህርትና ስልጠና የማብቃትና ሁለንተናዊ አካታችነትና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review