አዲስ አበባ ላይ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing አዲስ አበባ ላይ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑ ተገለጸ

AMN – ሰኔ 30/ 2017ዓ.ም

‎ለሃገሪቱ ሁለንተናዊ እድገትን ለማረጋገጥ እና ለዳበረ ዴሞክራሲዪዊ ስርአት ግንባታ ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል::

ለሲቪክ ማህበራት አባላትና አመራሮች በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዙሪያ በቂረቆስ ክፍለ ከተማ አዳራሽ ስልጠና ተሰጧል::ስልጠናውንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ሰጥተዋል፡፡

በስልጠና መድረኩም የብልፅግና ፖርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻና ምክትል ሀላፊዋ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሺፈራው ተገኝተዋል::

‎አቶ ሞገስ ባልቻ ለዳበረ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና አገር እድገት መንግስትና ሲቪክ ማህበራት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::ሲቪክ ማህበራቱም በአዲስ አበባ ከተማ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሚደንቅና ከዚህ በፊት በነበሩ መንግስታት ሊሰራ ቀርቶ ፍፁም ያልታሰበ እንደነበር አንስተዋል::

‎በአዲስ አበባ ብቻ ከ9 ሺህ በላይ የሲቪክ ማህበራት የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በርካታ የመረዳጃ እድሮች ይገኙበታል::የመረዳጃ እድሮች ምክር ቤትም እነዚህን እድሮች ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል::

‎አቶ ሞገስ ከሲቪክ ማህበራቱ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን መንግስትና ሲቪክ ማህበራቱ በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አውስተው በቀጣይም ተመሳሳይ የስልጠና መድረኮች እንደሚዘጋጁ አሳውቀዋል::

‎በየሺዋስ ዋለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review