የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሰሩ የህፃናት መጫዎቻዎች እና የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡
በክፍለ ከተማው 21 የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና 366 የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች መሰራታቸውም ተገልጿል።
በመርሐ-ግብሩም ህዝቡ ለፕሮጀክቶቹ ጥንቃቄ እያደረገ እንዲጠቀምባቸው ከንቲባዋ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከ 1 ሺህ በላይ የህፃናት ማቆያ እና መጫዎች እንዲሁም 122 የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በዛሬው እለት ተመርቀው ወደ አገልግሎት ይገባሉ።
በአይናለም አባይነህ እና አፈወርቅ አለሙ