የከተማ አስተዳደሩ መሬትን ከግለሰብ ተጠቃሚነት ወደ ህዝብ ተጠቃሚነት እየቀየረ እንደሚገኝ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ መሬትን ከግለሰብ ተጠቃሚነት ወደ ህዝብ ተጠቃሚነት እየቀየረ እንደሚገኝ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN – ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬትን ከግለሰብ ተጠቃሚነት ወደ ህዝብ ተጠቃሚነት እየቀየረ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ ።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት ማቆያ ስፍራዎችን መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ መርሐ-ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና የወጣቶች ተጠቃሚነት እንዲጎለብት እየሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደሩ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 122 የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውንም ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳድሩ መሬትን ከግለሰብ ተጠቃሚነት ወደ ህዝብ ተጠቃሚነት እየቀየረ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

አሁን የሚሠሩት የልማት ስራዎች ዘላቂነታቸው የተረጋገጠ እና የወጣቶችን ስብእና የሚገነቡ መሆናቸው የታመነበት እንደሆነም አመላክተዋል።

በከተማዋ የህፃናት እድገትን ማሻሻል እንደተቻለና ለዚህም የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ማሳያ መሆኑን ያነሱት አቶ ጃንጥራር፣ ዛሬ ወደ አገልግሎት የሚገቡት የህፃናት ማቆያ እና መጫወቻ ስፍራዎች የህፃናትን እድገት የሚረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

በወንድምአገኝ አበበ እና በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review