የመጀመሪያው ለህጻናት ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቀደ

You are currently viewing የመጀመሪያው ለህጻናት ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቀደ
  • Post category:ጤና

AMN – ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም

ለሕፃናት እና ለጨቅላ ህፃናት ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያው የወባ ሕክምና መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ተሰጥቶታል።

መድሃኒቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአፍሪካ ሀገራት ይሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም ለጨቅላ ህፃናት ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የወባ በሽታ መድሃኒት ያልነበረ እና ከመጠን በላይ የመውሰድ አደጋ ባለው መልኩ ከፍ ላሉ ልጆች በተዘጋጀ መድሃኒት ህክምና ይሰጥ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።

መድሃኒቱ ኖቫርቲስ በተባለ የስዊዘርላንድ መድሃኒት አምራች ኩባንያ የተመረተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፈረንጆቹ 2023 ከወባ በሽታ ጋር በተያያዘ ከተመዘገቡ 597 ሺህ ሞቶች መካከል ሶስት አራተኛ የሚሆኑት ከ5 ዓመት በታች የሚሆኑ ህፃናት መሆናቸው በዘገባው ተመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review