በማዕከላዊ ቴክሳስ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ100 ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ

You are currently viewing በማዕከላዊ ቴክሳስ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ100 ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ

AMN- ሐምሌ 02/2017 ዓ.ም

ባሳለፍነው ሳምንት በማዕከላዊ ቴክሳስ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 108 መድረሱን የግዛቲቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በጎርፍ አደጋው 10 የካምፕ ሚስቲክ ተጠላዮች እና አንድ አማካሪ አሁንም የደረሱበት እንዳልታወቀ እና የማፈላለጉ ስራ መቀጠሉን ፖሊስ አስታውቋል።

በኬር ካውንቲ የነበረው የሟቾች ቁጥርም ወደ 87 ከፍ ብሏል፣ በአቅራቢያ ባሉ ሌሎች የግዛቱ አካባቢዎችም በትንሹ 17 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ መመዝገቡን አር ቲ ኢ አስነብቧል።

የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪዎች አሁንም በአደጋው የጠፉ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ፣ በአከባቢው ያለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ የማፈላለግ ስራውን ከባድ እንዳደረገውም ተነግሯል።

በዚህም ምክንያት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።

የአሜሪካ የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በመጪው አርብ በአደጋው ጉዳት የደረሰበትን አከባቢ ለመጎብኘት ቀጠሮ መያዛቸውም ታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review