አረንጓዴ አሻራ ትውልድና ሀገርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የህዳሴ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ገለጹ

You are currently viewing አረንጓዴ አሻራ ትውልድና ሀገርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የህዳሴ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ገለጹ

AMN- ሐምሌ 02/2017 ዓ.ም

የህዳሴ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ሱራፌል እሸቱ አረንጓዴ አሻራ ትውልድና ሀገርን ታሳቢ ያደረገ ትልቅ ተግባር መሆኑን ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ገልጸዋል።

ባለፉት ዘመናት ባልተገባ መልኩ ደን በመጨፍጨፉ የሀገሪቱ የደን ሽፋን ተጎድቶ ድርቅና ተያያዥ ችግሮች በተለያዩ ወቅቶች መፈራረቃቸውንም ያስታውሳሉ።

አሁን ግን በጥቂት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ የደን ሽፋኑ እየተሻሻለ መጥቷል ብለዋል።

በመሆኑም አረንጓዴ አሻራ ከርዕዮተ ዓለም ወይም ከፖለቲካ እሳቤ ልዩነት ጋር የሚያያዝ አይደለም ያሉት ኢንጅነር ሱራፌል፣ ይልቁንም ለትውልድ ታስቦ የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

መሰል ለትውልድ የሚከወኑ ልማቶችን ከፖለቲካ ጋር ማያያዝ ተገቢነት የሌለው እሳቤ መሆኑን ገልጸዋል።

ፓርቲያቸውም በዚህ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ፋይዳ ባለው ተግባር ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን እና በቀጣይም አባላቱን በማስተባበር አሻራውን እያኖረ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በዚህ በጎ ዓላማ ላይ ፓርቲያቸው ያለውን ንቁ ተሳትፎ በማጎልበት ምርታማና በአየር ንብረት ለውጥ የማትናወጥ ሀገር በጋራ እንገንባ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

እሳቸውም በተለያዩ ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች በመሳተፍ የድርሻቸውን ያበረከቱ ሲሆን፣ በዘንድሮም መርሐ-ግብር ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review