ኪየቭ ምሽቱን በድሮን ጥቃት ተመታች

You are currently viewing ኪየቭ ምሽቱን በድሮን ጥቃት ተመታች

AMN- ሐምሌ 03/2017

የዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪየቭ ምሽቱን በሩሲያ ድሮኖች መመታቷን የከተማዋ ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

ጥቃቱ ማዕከላዊ ሼቭቼንኪቭስኪ ዲስትሪከት ተብሎ በሚጠራው የከማዋ ሥፍራ ላይ በሚገኝ መኖሪያ ህንፃ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በምሽቱ ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 13 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ዩክሬን በበኩሏ በባሊስቲክ ሚሳኤል የታገዘ አፀፋዊ ጥቃት ልትፈፅም እንደምትችል አስጠንቅቃለች፡፡

ሩሲያ ምሽቱን በኪየቭ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አስመልክቶ የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡

ዩክሬን ማክሰኞ እለት በ728 ድሮኖች እና 13 ክሩዝና ባሊስቲክ ሚሳኤሎች በተለያዩ ከተሞቿ የተፈፀመባት ጥቃት ከእስካሁኑ ሁሉ የከፋ ነው ስትል መግለጿን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review