ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

You are currently viewing ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

AMN ሐምሌ 3/ 2017 ዓ.ም

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዕድገት ያለዉ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምረ ኮንፈረንስ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነዉ፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ምርምር ለማንኛውም ሀገራዊ ልማትና ዕድገት መሠረት ነው ብለዋል፡፡

ምርምሮች ችግሮች በሚያገኘው ጊዜ ከመፍታት ባለፉ አዳዲስና አማራጮችን መፍትሄምን ለመጠቆም እንዲሁም ዕውቀት ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ለመወስን የሚያስችል ነው ብለዋል።

የጥናትና ምርምር ባህልን በማዳበር ልህቀትን በተግባር ማዋል ቀጣይነት ላለው ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ አውጪ እንደመሆኑ መጠን የሚያወጣቸው ህጐች፣ የሚወሰናቸው ውሳኔዎች እና አፈፃፀምቹ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ በማንሳት በዚህም መሠረት ጥናትና ምርምሮች ለህግ አውጪው አካል ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

የዘንድሮ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ለ5ኛ ጊዜ “ፓርላማዊ ተግባራትን ማጠናከር ለአካታች አስተዳደር ፣ ለሀገር በቀል ዕውቀትና ለዘላቂ ልማት ! ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ዳይሮክተሬት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review