በበጀት አመቱ 4 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሃብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በበጀት አመቱ 4 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሃብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN-ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም

በበጀት አመቱ 4 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሃብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ የበጀት ዓመት ማጠቃለያ ጉባዔውን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለምክር ቤቱ የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም እና የ2018 የስራ እቅድ አቅጣጫዎች ላይ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ዘርፉን በፍትሃዊነት በማሳደግ በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ተማሪዎች የትምህርት ቅበላቸው እንዲያድግና በጨዋታ መልክ እንዲማሩ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸዉንም ገልጸዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ፍታዊነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የልዩ ፍላጎት ትምርት የሚከታተሉ 34 ሺ 15 ተማሪዎችን መቀበል መቻሉንም ተብራርቷል፡፡

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል ጋር በተያያዘም መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ልዩ ትኩረት መነሻ በማድረግ 4 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሃብት በማሰባሰብ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደተቻለም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል፡፡

ከምገባ ጋር በተያያዘም ከ840 ሺ 585 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለቴ እንዲመገቡ መደረጉን በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡

በበጀት አመቱ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ ክፍል እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ሙሉ ለሙሉ መሳካት መቻሉንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ገልፀዋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review