16 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች የሰረቁ አምስት ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing 16 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች የሰረቁ አምስት ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN ሐምሌ 05/2017 ዓ/ም

ከጥበቃ ሰራተኛ ጋር በመመሳጠር 16 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ አምስት ወንጀል ፈፃሚዎችን ከነ ጥበቃው በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቶቹን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ12 ልዩ ቦታው ቡልቡለ ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ንብረትነታቸው የሶፍ ኡመር ትሬዲንግ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሆኑ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት A 08160 እና ኮድ 3 ኢት A 07564 የዋጋ ግምታቸው 16 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎችን ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ ከቆሙበት ሰርቀው መሰወራቸዉን ገልጸዋል፡፡

የተሽከርካሪዎቹ መሰረቅ መረጃ የደረሰው የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ክትትልና ባሰባሰበው መረጃ የስርቆት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግስቱ ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 11 ሰዓት አንዱን ሲኖትራክ በመቂ ከተማ እንዲሁም ሌላውን ደግሞ አዳሚ ቱሉ (ዝዋይ ) ከተማ ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቱን ማስመለሱን ገልጸዋል፡፡

የጥበቃ ሰራተኛውን ጨምሮ በወንጀሉ ተሳትፎ ያላቸው ስድስት ወንጀል ፈፃሚዎችን ጨምሮ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጠቁመዋል፡፡

ዋና ወንጀል ፈፃሚ የሆነው ከበደ ቆሪቾ የተባለውን የድርጅቱ ተረኛ ጥበቃ ሰራተኛ ሁለት ሚሊዮን ብር እንሰጣለን ስላሉት ወንጀሉን እንደፈፀሙና የጥበቃ ሰራተኛውም ኃላፊነቱን ወደ ጎን በማለት ተባባሪ ሆኖ ወንጀሉን ማስፈፀሙን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታውቋል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review