የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቀቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቀቀ

AMN-ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት፦

1. አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ፣

2. አቶ መኮንን ያኢ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ፣

3. አቶ ኦሊያድ ስዩም የከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዳዩች እና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ የቀረቡ ሲሆን ምክርቤቱም የቀረቡትን እጩዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review