አስተዳደሩ የቱሪዝም ኮሚሽንን በአዲስ መልክ አቋቋመ

You are currently viewing አስተዳደሩ የቱሪዝም ኮሚሽንን በአዲስ መልክ አቋቋመ

AMN- ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበዔውን 2ኛ ቀን ውሎ በአድዋ ድል መታሰቢያ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ አዳምጦ ሰፊ ውይይት ካደረገበት በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁን የፍትህና የመልካም አስተዳዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝግጅት ሂደት ከከንቲባ ፅ/ ቤትና ከፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመሆን አለም አቀፍ እና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በልዩ ትኩረት መሠራቱ ተገልጿል።

ቱሪዝም ቀጣይ የከተማዋ የልማት የትኩረት አቅጣጫ፥ የስራ እድል ፈጠራ ማዕከል ዘርፍ፥ እንዲሁም በቀጣይ የቱሪዝም መዳረሻ ልማቶችን በስፋት ማስተዋወቅ እና የውጪ ምንዛሬ ማስገኛ ስትራቴጂክ ዘርፍ በመሆኑ እና መዲናዋ አለም አቀፍ የንግድ ፥ የባህል እና የቅርስ ቱሪዝም መዳረሻ የመሆን አቅም ያላት እንደመሆኗ ዘርፉን በአዲስ መልክ በኮሚሽን ደረጃ በማደራጀት እንዲመራ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም ኮሚሽን በተቋም ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review