የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

AMN- ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በምክር ቤቱ ፀድቋል፡፡

ረቂቅ በጀቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አማካኝነት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

በቀረበው ረቂቅ ላይ አጠቃላይ 350.13 ቢሊየን ብር በምን መልኩ ለማግኘት እንደታሰበ ተዘርዝሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከታክስ ገቢ 238 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ አቶ አብዱልቃድር አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ በጀቱ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review