ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤኒሻንጉል አሶሳ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤኒሻንጉል አሶሳ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

AMN-ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ማምሻዉን የምዕራቧ ኮከብ በሆነችው በቤኒሻንጉል አሶሳ ከተማ ከወንድሜ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል” ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም በአሶሳ ከተማ “ሀለዋ የአግሮ ኢንዱስትሪ” መንደር በ60 ሄክታር ላይ ያረፈውን የሌማት ቱሩፍት የሆነውን የዶሮ ፣ የእንቁላል እና የወተት ተዋፅኦ በቀላል መንገድ በማልማትና የአካባቢ ሀብትን በመጠቅሞ እንዴት ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ተዘዋውረን ጎብኝተናል ብለዋል።

አዲስ አባባ ከክልሎች ጋር የምርት አቅርቦት ትስስር በመፍጠር ምርትን ወደ ከተማዋ እንዲገባ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ከንቲባዋ በቀጣይም በኮሪደር ልማት የተሰሩትን ስራዎች ልምድ ልውውጥም እንደሚደረግ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአሶሳ ስለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review