22 ሺህ የሚሆኑ አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላትን ለማስመረቅ ዝግጅት ተጠናቋል – ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

You are currently viewing 22 ሺህ የሚሆኑ አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላትን ለማስመረቅ ዝግጅት ተጠናቋል – ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

AMN – ታኀሣሥ 16/2017 ዓ.ም

የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ ወጣቶችን ያሳተፈ 22 ሺህ የሚሆኑ አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብና የአካል ብቃት ስልጠና በመስጠት ለማስመረቅ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃለፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ የአደረጃጀት ዘርፍ አዲስ ሰልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላት በንድፈ ሀሳብና በተግባር ስልጠና ለሚሰጡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ኦረንቴሸን ሰጥቷል።

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፣ የጸጥታ ስራ በጸጥታ መዋቅር ብቻ መስራት የሚቻል አይደለም፡፡

በመሆኑም ቢሮው ማህበረሰቡን በማሳተፍ የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ ወጣቶችን ያሳተፈ 22 ሺህ የሚሆኑ አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብና የአካል ብቃት ስልጠና ሰጥቶ ለማስመረቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኃላፊዋ መናገራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review