የአውሮፓ ሕብረት እና ሜክሲኮ የትራምፕን 30 በመቶ የቀረጥ ጭማሪ ዕቅድ ተቹ

You are currently viewing የአውሮፓ ሕብረት እና ሜክሲኮ የትራምፕን 30 በመቶ የቀረጥ ጭማሪ ዕቅድ ተቹ

AMN- ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ2 ሳምንታት በኋላ በአውሮፓ ሕብረትና ሜክሲኮ ላይ የቀረጥ ጭማሪ ለመጣል እቅድ መያዛቸው ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም የአውሮፓ ሕብረትና ሜክሲኮ በፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ደስተኛ አለመሆናቸውን በመግለፅ የቀረጥ ጭማሪውን ተችተዋል፡፡

ሜክሲኮ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብ ገልፃለች፤ የአውሮፓ ሕብረት በበኩሉ እንደ አስፈላጊነቱ ተመጣጣኝ የሆነ አፀፋዊ ምላሽ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ ይሁንና ከአሜሪካ ጋር ንግግር መቀጠል እንደሚፈልጉም ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔውን ከመቀበል ይልቅ ሌላ አማራጭ የሚከተል ካለ ግን የታሪፍ ጭማሪው ከዚህም ይብሳል ነው ያሉት፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ካናዳ እና ከብራዚል ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ ታሪፍም ፕሬዝዳንቱ ይፋ አድርገዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review