የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሀመዱ ቡሃሪ በ82 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
ቡሃሪ ከሶስት ተከታታይ የምርጫ ወቅቶች ሽንፈት በኋላ በ2015 ድል የቀናቸው የመጀመሪያው ተፎካካሪ ፓርቲ መሪ ነበሩ።
በ2015 የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ለመሆን የበቁት ቡሃሪ በፈረንጆቹ 2019 ለ2ኛ ጊዜ ተመርጠው ሀገሪቱን በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።
ቡሀሪ በተደጋጋሚ ጊዜ ጤናቸውን ለመታየት ወደ ለንደን ይሄዱ የነበረ ሲሆን ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ለንደን እንዳቀኑ ተሰምቷል።
በዛሬው እለትም ህክምና በሚከታተሉበት ክሊኒክ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
በማሬ ቃጦ