በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

You are currently viewing በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

AMN – ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በ2017 በጀት ዓመት 1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ ሲሰራ መቆየቱን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ ተናግረዋል።

በቅንጅት በተሰራው ሥራ 4 ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የተናገሩት ሃላፊው፤ ውጤቱም ከታቀደው በላይ ሶስትና አራት እጥፍ እንደሆነ ተናግረዋል።

መንግስት ለወርቅ አቅራቢዎች ያደረገው ማበረታቻ እና ህገ-ወጥ ግብይት መቀነስ ለተመዘገበው ውጤት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ሃላፊው አስታውቀዋል።

በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘርፉ እንዲነቃቃ እና አምራቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የተመረተው ወርቅ በአነስተኛ እና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች መሆኑን የተናገሩት አቶ አድማሱ፤ ይህም የህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደጉን አመላክተዋል።

ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰል እና እምነበረድ በስፋት እየተመረተ መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው፤ በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

ከማዕድን በሚገኝ ገቢም 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡን ሃላፊው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review