የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት በድሬዳዋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፤ የዋና ጽ/ቤትና የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፣ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት መሪ ዕቅድ ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።